Sunday, May 30, 2010

መለከት

ካህናቱም በየሥርዓታቸው፥ ሌዋውያኑም ደግሞ። ምሕረቱ ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ የሚለውን የዳዊትን መዝሙር እየዘመሩ፥ ንጉሡ ዳዊት እግዚአብሔርን ለማመስገን የሠራውን የእግዚአብሔርን የዜማ ዕቃ ይዘው ቆመው ነበር ካህናቱም በፊታቸው መለከት ይነፉ ነበር እስራኤልም ሁሉ ቆመው ነበር። መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 7:6
የማንም እጅ አይንካ ነገር ግን የሚነካው ሁሉ ይወገራል፥ ወይም በፍላጻ ይወጋል እንስሳ ወይም ሰው ቢሆን አይድንም በላቸው። ሳያቋርጥ የመለከት ድምፅ ሲነፋ በዚያን ጊዜ ወደ ተራራው ይውጡ................
እንዲህም ሆነ በሦስተኛው ቀን በማለዳ ጊዜ ነጐድጓድና መብረቅ ከባድም ደመና እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምጽ በተራራው ላይ ሆነ በሰፈሩም የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተንቀጠቀጡ። ኦሪት ዘፍጥረት 19:13-16
ሙሴም ከየነገዱ አንድ አንድ ሺህ ወደ ጦርነት ሰደደ እነርሱንና የካህኑን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን ወደ ጦርነት ሰደዳቸው የመቅደሱንም ዕቃ የሚነፋውንም መለከት በእጁ ሰጠው።ኦሪት ዘኍልቍ 31:6

Tuesday, May 25, 2010

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን።

ጻድቃን ሆይ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ለቅኖች ምስጋና ይገባል። እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፥ አሥር አውታርም ባለው በበገና ዘምሩለት። አዲስ ቅኔም ተቀኙለት፥ በእልልታም መልካም ዝማሬ ዘምሩ፤ የዳዊት መዝሙር። 33: 1-3

ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት፤ በኃይሉ ጠፈር አመስግኑት።በችሎቱ አመስግኑት፤ በታላቅነቱ ብዛት አመስግኑት።በመለከት ድምፅ አመስግኑት፤ በበገናና በመሰንቆ አመስግኑት።በከበሮና በዘፈን አመስግኑት፤ በአውታርና በእምቢልታ አመስግኑት። ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት፤ እልልታ ባለው ጸናጽል አመስግኑት እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን። ሃሌ ሉያ።የዳዊት መዝሙር150:1-6

Monday, May 24, 2010

mezmur

ወደ ባሕር የምትወርዱ በእርስዋም ውስጥ ያላችሁ ሁሉ፥ ደሴቶችና በእነርሱም ላይ የምትኖሩ ሆይ፥ ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር፥ ከምድርም ዳርቻ ምስጋናውን ዘምሩ።